ስለ

ሚኒስቴሩ

በኢትዮጵያ ከትላልቅ እስከ መካከለኛ እርሻዎችን ለማልማት መስኖ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። ይሁን እንጂ ለአገሪቱ የግብርና ዘርፍ እና አጠቃላይ የኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ከሚፈጥረው ዕድል አንፃር ሲታይ አሁንም የሚጠበቀውን ያህል ጥቅም ላይ አልዋለም። በተጨማሪም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2023 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ባስቀመጠችው ግብ መሰረት የተፈጥሮ ሀብትና የመስኖ ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም ይህንን ራዕይ እውን ለማድረግ ያስችላታል።
ተጨማሪ ያንብቡ

መመሪያ

ከግብርና እና ውሃና ኤነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባባር የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ውሃን ማዕከል ያደረጉ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ የመስኖ ልማቶች እንዲስፋፉ ያደርጋል፤

በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት በውሃና ኤነርጂ ሚኒስቴር ጥናት የተለዩ የሀገሪቱን የከርሰ ምድር እና የገጸ-ምድር የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት የሚውልበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤

የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ምርታማነት በሚያሳድጉ ወቅታዊ ቴክኖሎጂዎች እንዲደገፉና ውሃ ቆጣቢ አሠራር እንዲከተሉ ያበረታታል፤

የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ እንዲያገኙ በተለያዩ ዘዴዎች ያስተዋውቃል፤ ሕግን መሠረት በማድረግ ባለሀብቶች ማትጊያ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤

አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያስተባብራል፤

በተፋሰሶች ውስጥ የሚደረጉ የመስኖ ማስፋፋት ሥራዎችን ለመደገፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል፤

ሚኒስቴሩ

የክቡር ሚኒስትሯ መልዕክት

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን እንዲሁም ራስን በራስ የማስተዳደር አቅምን ለማረጋገጥ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት መስራት ጀምራለች።

ድርቅን ለመቋቋም፣ የአየር ሁኔታና የአየር ንብረት ለውጥን አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ለመከላከል የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር (MILLs) ዘላቂ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ቀጣይነት ያለውና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የመስኖ መርሃ ግብሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ታላቅ ግቦችን አስቀምጧል። ይህም በሀገራችን ከመካከለኛ እስከ ትልቅ ግብርና እንቅስቃሴዎችና የምግብ ምርት ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል። በተጨማሪም ሚኒስቴሩ ውሃን እንደ ዋና ግብዓት በመጠቀም አዳዲስ፣ የተቀናጁና ዘላቂ የልማት መፍትሄዎች በመጠቀም የቆላማ አካባቢዎችን ልማትና አስተዳደር የማዘመን ግቦች አሉት።

የምግብ ምርትን በቴክኖሎጂ በታገዘ የመስኖ ልማት እንዲሁም የተቀናጀና ዘላቂ የቆላማ አካባቢ ልማትን በማስፋፋት ማሻሻል ይቻላል። ይህም ረሃብና ድህነትን ለማስወገድና የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ስልት ነው ብዬ አምናለሁ። በመሆኑም በአዲሱ የኢፌዲሪ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎችን በመመርኮዝ ነባር የመስኖ ስርዓትና የቆላማ ልማት ስራዎችን ለማቀላጠፍ እና ለማዘመን የበለጠ ጥረት እያደረግን ነው።

ለእነዚህ መሰል ዓላማዎች ግብ መምታት ሚኒስቴሩ የሀገር ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ እና የመንግስት ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያስፈልገዋል። በእነዚህ የለውጥ ጉዞዎች የምግብ ሉዓላዊነትን እና የቆላማ አካባቢ ልማትና አስተዳደርን ለማስፈን እንዲሁም በርካታ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የመንግስት አቻዎቻች እንዲሁም የግሉ ሴክተር የልማት አጋሮቻችን እንድትሆኑ በአክብሮት እጋብዛለሁ።

ክብርት ኢ/ር አይሻ መሀመድ ሙሳየመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትርየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር

አጋሮቻችን

በራሪ ጽሑፍ

የግንዛቤዎችና የጉዞአችን አካል ለመሆን ይመዝገቡ!