News
Get in Touch
English
The Ministry
Irrigation Development Sector
Projects
Lowland Development Sector
Administration sector
Publications
Search
News
Get in Touch
English
In
News
•
August 16, 2024
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ስታንዳርድና ደንብ ዶክመንት ዝግጅትን የስራ ሂደት ገመገመ ************************ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ስታንዳርድና ደንብ ዝግጅት አፈጻጸም ያለበትን ሂደት የሚኒስቴር መ/ቤቱና የፕሮጀክቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በሚኒስቴር መ/ቤቱ አዳራሽ በቀን 9/12/2016 ዓ/ም ገምግሟል፡፡ ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር እንዳሉት የመስኖ ስታንዳርድና ደንብ መኖር መስኖን እንደ ተቋምና ዘርፍ ሊያሳድገው የሚችል ተግባር በመሆኑ በልዩ ትኩረትና ጥራት ሊሰራ ይገባል፡፡ የመስኖ ስታንዳርድ ለማዘጋጀት ፕሮጀክት ይፋ የተደረገው ባለፈው ታህሳስ 2016 ዓ.ም ሲሆን ዋነኛ ዓለማውም በዲዛይንና ጥናት፣ በግንባታና በመስኖ የመሰረተ-ልማት አገልግልትና አገልግሎት አሰጣጥ ያለውን ችግር በመቅረፍ ጥራት ያለውና ወጪ ቆጣቢ የመስኖ ዘዴዎችንና አሰራሮችን በመተግበር ምርትና ምርታማነትን መጨመር እንዲያስችል ነው፡፡ የመስኖ ስታንዳርዱ የሚዘጋጀው ከFAO በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን አዘጋጁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ ከኢትዮጵያ ስታንዳርድ ኢንስቲትዩት እና ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው፡፡ ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም
Privacy Preference Center
Privacy Preferences
This site is registered on
wpml.org
as a development site.